በሐዋሳ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤተክርስቲያን ከየካቲት 18-22/2012 ዓ/ም በነበረዉ ዓመታዊ የእህቶች ኮምፈራንስ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ስልጠና በቤተሰብ አድን አገልግሎት ለቤተሰብ መሪዎች የተሰጠ ሲሆን 21-22/6/ 2012 ዓ/ም ባለዉ ጊዜ ለባሎችና ለሚስቶች ለወጣቶች ትምህርት የተሰጥቱዋል፡፡ ለቤተሰብ ጸሎትና ባሎችና ሚስቶች፣ ወላጆች ለልጆችን ቡራኬ ጊዜ ተደርጉዋል፡፡ በዚህ ኮምፍራንስ በአከባቢ ስላሌዉ የቤተሰብ ሁኔታ ስለ ጋብቻ ፍቺ፣ ልጆች ለወላጆች ያለመታዘዝ ችግሮች፣ የቤተሰብ መንፈሳዊ ሕይወት መሞት እያስከተለ ያለዉ ችግር፣ በልጆች አያያዝና አስተዳደግ የሚታዩ ችግሮች የተዳሰሱ ሲሆን የጉባኤ አባላት ስለ ቤተሰብ አድን አገልግሎት እና ራዕይ እግዚአብሔርን አመስግነዋል፡፡ ከ400 በላይ የቤተሰብ አድን አገልግሎት ቤተሰብን ደቀ መዝሙር የማድረግ ዘዴ አንደኛ መጽሐፍ በቤተሰብ የሚጠና ስለሆነ የማግኘት ዕድል ተፈጥሮ በታላቅ ደስታ በንስሐና በጸሎት ተጠናቁዋል፡፡