በአረካ ከተማ ከወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ጋር በመተባበር ቤተሰብ አድን አገልግሎት ከጥር 5-6/2015 ዓ/ም ኮምፍራንስ ተካሄደ፡፡ በዚህ ኮምፍራንስ ስለ ጋብቻ መበላሸት፣ ቤተሰብ ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ካለማድረግ የተነሳ መንፈሳዊ ሕይወት እየሞተ በመሆኑ በቤተሰብ መካከል እየተፈጠሩ ስላሉ ችግሮች እና ቤተሰብ አድን አገልግሎት የማገልገል ዘዴ፣ የጋብቻ ፍቺ ምክንያቶች ትምህርት የተሰጥቱዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተደረገዉ የጸሎትና የፈዉስ ጊዜ ብዙዎች ከእስራት የተፈቱ ሲሆን ስለቤተሰብ ንስሐ በመግባት ከሚሄዱበት የጥፋት መንገድ ብዙዎች መመለስ ችለዋል፡፡ በመጨረሻም ቤተሰብን ለእግዚአብሔር መንግሥት ለማዘጋጀት፣ የቤተሰብ እምልኮ ለማካሄድ ቃል በመግባት በታላቅ የእግዚአብሔር መገኘት በደስታ እና በምስጋና ተጠ ናቁዋል፡፡