በወላይታ ሶዶ ከተማ " መፋታትን እጠላለሁ ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር" በሚል መሪ ቃል የጋብቻ ፍቺ በመቃወም ሰኔ 22/2015 ዓ/ም ኮምፍራንስ ተካሂዱዋል፡፡
በአለማችንና በምድራችን የጋብቻ መበላሸት (ግብረ ሰዶም፣ ኮንትራት ጋብቻ፣ የመሳሰሉት) በተለይም የጋብቻ ፍቺ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑ አሳዛኝ እየሆነ መጥቱዋል፡፡ ይህን ሁኔታ ለሚመለከታቸዉ አካላት ግንዛቤ መፍጠርና መቃወም ተገቢ ስለሚሆን በከተማዉ የጋብቻ ፍቺ መቃወም ከፍተኛ አዋጅ የታወጀ ሲሆን፣ " መፋታትን እጠላለሁ ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር " የሚል መሪ ቃል ባኔር በማዘጋጀት በየጎዳናዉ በመለጠፍ ብዙዎች እንዲያነቡ ከመደረጉም በተጨማሪ ለጉባኤ ትምህርት የተሰጠ ሲሆን የፓናል ዉይይት በማድረግ ሰፍ ግንዛቤ የመፍጠር አገልግሎት ተሰጥቱዋል፡፡