በቦዲቲ ዕድገት ቃለ ሕይወት ቤ/ያን ቤተሰብ አድን አገልግሎት መጽሐፍን ለ3 ወራት አጥንተዉ የጨረሱ 22 የቤተሰብ መሪዎች የካቲት 15/2016 ተመረቁ፡፡ በአለም አቀፍ ቤተሰብ አድን አገልግሎት ስልጥነዉ የሚያሠልጥኑ (ቲኦቲ) የቤተክርስቲያን ሰልጣኞች መካከል በቦዲቲ ከተማ ዕድገት ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የቤተሰብ አድን አገልለሎት ቤተሰብን ደቀ መዝሙር ማድረግ ዘዴና ትምህርቶቹ አንደኛ መጽሐፍ ለ3 ወር አጥንተዉ የጨረሱት ባለትዳሮች እሁድ ባለዉ አምልኮ ፕሮግራም ለሌሎች ትምህርት በሚሆን መልክ የአለም አቀፍ ቤተሰብ አድን አገልግሎት ቦርድ አባላት በተገኙበት በሠርትፍኬት ተመርቀዋል፡፡ ሰልጣኞች በጥናቱ ስለ ቤተሰብ ግንዛቤ የፈጠሩና ቤተሰቦቻቸዉን ለእግዚአብሔር መንግስት ለማዘጋጀት የሚያስችል ትምህርት እንዳገኙ የገለጹ ሲሆን ፤ የቤተክርስቲያን መሪዎችም ያጠኑ አባላት ሌሎችን ማሰልጠን የሚችሉ በመሆናቸዉ ለቤተክርስቲያን ጠቃሚ ስለሆነ እንደሚያስቀጥሉ ተናግረዋል፡፡