በሳዱዬ ቃለ ሕይወት ቤ/ያን በተደረገው ኮምፍራንስ ቤተሰብ አድን አገልግሎት ትምህርት ተሰጠ፡፡ በሶዶዬ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የካቲት 16-18/2016 ዓ.ም. ሦስት ቀን በተዘጋጀ ኮምፍራንስ ስለ ቤተሰብ አድን አገልግሎት ትምህርት የተሰጠ ሲሆን ፣ የቅድመ ጋብቻና የጋብቻ በመላሸት፣ ወላጆች ከልጆች ጋር ስላለዉ አስከፍ ሁኔታ፣ በቤተሰብ ወንጀል እየተፈጸመ መምጣት፣ ፈርሃ እግዚአብሔር እየጠፋ መምጣት፣ አሁን ቤተክርስቲያን ስላለችበት ሁኔታ ትምህርት በመሰጠቱ አገልጋዮችን ጨምሮ ጉባኤዉ በእግዚአብሔር ፊት ወድቆ ንስሐ የገባ ሲሆን የጌታ መምጣት በደጅ ስለሆነ ቤተሰብ እንድዘጋጅ እግዚአብሔር ያሳሰበን ጊዜ ነዉ በማለት በታላቅ ደስታ እግዚአብሔርን በማመስገን ተጠናቁዋል፡፡