latest news
Post Content Holder
የቦንኬ ቃለ ሕይወት አጥቢያዎች ሕብረት ከሰኔ 15-16 /2016 ዓ/ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት ቤተሰብ አድን አገልግሎት ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቱዋል
የቦንኬ ቃለ ሕይወት አጥቢያዎች ሕብረት ከሰኔ 15-16 /2016 ዓ/ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት ቤተሰብ አድን አገልግሎት ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቱዋል
Visit our website for latest News

የቦንኬ ቃለ ሕይወት አጥቢያዎች ሕብረት ከቀን 15-16 /10/2016 ዓ/ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት ከ60 አጥቢያ ወ = 125 ሴ =4 ድ = 129 የአጥቢያ መሪዎች፣ ሴቶች፣ ወጣቶችና አገልጋዮች (መጋቢያንና ወንጌላዊያን) ቤተሰብ አድን አገልግሎት ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቱዋል፡፡
ከስልጠናዉ በሁዋላ እያንዳንዱ ሰልጣኝ የቤተሰብና የቤተክርስቲያን ተደራራቢ ኃላፍነት ያለበት ስለሆነ በየቤታቸዉ ከቤተሰብ አባላት ጋር ለማጥናትና በአጥቢያቸዉ ስለጠና ለመስጠት ቤተሰብ አድን አገልግሎት የቤተክርስቲያንና የቤተሰብ ሚና ሁለተኛ መጽሐፍ ይዘዉና ስልጠናዉን የሚከታተል ኮሚቴ ወክለዉ ተመልሰዋል፡፡
የቦንኬ አጥቢያዎች ሕብረት በነበረዉ ስልጠና ሰልጣኞች ስለቤተሰብ ንስሐ በመግባት ታላቅ ጸሎት የተደረገ ስሆን በስልጠናዉ መጨረሻ የነበረዉ ድባብ እያንዳንዱ ሰልጣኝ በስልጠና አዳራሽ ፊት ለፊት ተራ በተራ እየወጣ በመተቃቀፍ ሰላምታ እየሰጠ ይሰለፋል፡፡ ስለስልጠናዉና እግዚአብሔር ስለሰጣቸዉ ጊዜ በባህላዊ ዝማሬ እግዚአብሔርን በማማስገን ደስታቸዉን እየገለጹ ሰልጣኝ ሁሉ ሠላምታ ተለዋወጠው የሕብረቱ መሪዎችን ካሰናበቱ በሁዋላ ተሰነባብተዋል፡፡